ሞመንተስ ፋርማሲዮቲካል አ.ማ
MOMENTOUS PHARMACEUTICALS SC
ማሳሰቢያ፡-
- ቅጹ በሁለት ተሞልቶ ማህተም አርፎበት አንድ ኮፒ አክሲዮን ለገዛው አካል ሁለተኛ ኮፒ በሻጭ ባንክ ውስጥ መቀመጥ አለበት።
- አክሲዮን የሚገዙ ግለሰቦች፡-
- የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ማቅረብ አለባቸው
- በልጆች ስም ለመግዛት የሚፈልግ የልደት ካርድ እና የአባት/እናት/ወይም የአሳዳጊ መታወቂያ ማቅረብ አለባቸው
- አክሲዮን ለሚገዙ ድርጅቶች፡-
- የድርጅቱ የታደሰ ንግድ ፈቃድ/የንግድ ምዝገባ/የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር
- አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችል ህጋዊ ውክልና
- ማህበራት እና ዕድሮች የተመሠረቱበት የፈቃድ ሠርተፊኬት
- የተዘጋጀውን ቅጽ ሁለት ኮፒ ሞልተው የአክሲዮን ሽያጭም ሆነ አስተዳደራዊ ወጪ መሸፈኛ 5% ገንዘብ ሲያስገቡ የሞሉትን ቅጽ አንዱን እና በተራ ቁጥር 3 (ለግለሰብ ባለአክሲዮን) እና በተራ ቁጥር 4 (ለድርጅት ባለአክሲዮን) የተዘረዘሩትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ለባንኩ ሠራተኛ ያስረክባሉ፡፡
- የአክሲዮን ግዥ በተመለከተ፡-የአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ሆኖ አንድ ግለሰብ መግዛት የሚችለው ዝቅተኛው የአክሲዮን ብዛት 1(አንድ) ወይም 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ብዛት 700 (ሰባት መቶ) ወይም 10,500,000.00 (አስር ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር) ነዉ።
- ከአስር ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር በላይ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች/ድርጅቶች/ብሩን ገቢ ከማድረጋቸው በፊት በቅድሚያ ዋናው መ/ቤት ማነጋገር አለባቸው፡፡
- አክሲዮን ገዢዎች ክፍያቸውን በቀጥታ ከዚህ ቅጽ ጋር አባሪ በሆኑት ባንኮች በአንዱ ባንክ ሂሳቦች ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ለወኪሎች ወይም ለአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡
- የተከፈለው የአገልግሎት ክፍያ (service charge) ለአክሲዮን ገዢው ተመላሽ አይደረግም፡፡
- ሂሳብ ገቢ ማዘዣ ሰነድ ኮፒው ቀሪ ሆኖ ዋናው ለአመልካች ይሠጣል፡፡
- የአገልግሎት ክፍያ(service charge) የሚሠላው በተፈረሙ (Subscribed) አክሲዮኖች መጠን ሆኖ ክፍያውም ሙሉ ከመጀመሪያው ክፍያ ጋር ተጠቃሎ የሚፈጸም ይሆናል፡፡ነባር ባለአክሲዮኖች በየዓመቱ ከሚከፈለው መጠን ጋር ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በባለ አክሲዮኖች የተፈረሙ አክሲዮኖች ዋጋ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠቃሎ ለባንክ መከፈል አለበት፡፡በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያ ያልተፈጸመባቸውን አክሲዮኖች በተመለከተ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ድንጋጌ መሠረት ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡
- በዚህ ውል ላይ የተጠቀሰው አክሲዮን ግዥ እና የአገልግሎት ክፍያ ባንክ ገቢ ካልተደረገ እና በውሉ ላይም የባንኩ አርማ ያለበት ማህተም ካላረፈበት ዋጋ አይኖረውም፡፡
- ኢትዮጵያዊነትን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ካርድ፣ውክልና ስልጣን የሰነድ ማስረጃ፣የተገናዘቡ ኮፒዎች ከዚህ የማመልከቻ ቅጽ ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከሞመንተስ ፋርማሲዮቲካል አ.ማ ዋና መ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0996 76 76 76 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሞመንተስ ፋርማሲዮቲካል አክሲዮን ሽያጭ የሚገኙባቸው ባንኮች
- አቢሲንያ ባንክ
- ዘመን ባንክ
- አዋሽ ባንክ
- አማራ ባንክ
- ዳሽን ባንክ
- ኦሮሚያ ባንክ
- ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና
- ህብረት ባንክ